Posts

Showing posts from December, 2017

ወጥቶ የቀረው ኢትዮጵያዊው የጥበብ ሊቅ- ገብረክርስቶስ ደስታ

Image
ለዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ኢትዮጵያዊ ጥበበኛ፣ ኢትዮጵያን እጅግ የሚወዳት፣ በኢትዮጵያ የሥዕል እና የሥነ-ግጥም ዓለም ውስጥ ድምቅምቅ ብሎ ሁሌም ስሙ ስለሚጠራው ስለ ታላቁ ጥበበኛችን ስለ ገብረክርስቶስ ደስታ ነው። ገብረ ክርስቶስ ደስታ “ስሞት ሀገሬ ቅበሩኝ” እያለ በግጥም እየተቀኘ ሲማፀን የኖረ ባለቅኔ ቢሆንም፤ ሞቶ የተቀበረው ግን በባዕድ ሀገር ነው። ገብሬ “ሀገሬ” ብሎ ሲቀኝ እንዲህ አለ፡- ውበት ነው አገሬ ገነት ነው አገሬ ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ ባሳብ እሄዳለሁ ቢሰበርም እግሬ አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ። አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ “ብሞት እሔዳለሁ ከመሬት ብገባ” እያለ የዛሬ 50 ዓመት ግጥም የፃፈ ሰው ዛሬም አፅሙ በምድረ አሜሪካ ነው። ዛሬ ስለ ጥበበኛው ገብረክርስቶስ ደስታ ጥቂት ነጥቦችን እንጨዋወታለን። ገብረክርስቶስ ደስታ ጥቅምት 5 ቀን 1924 ዓ.ም በሐረር ከተማ አደሬ ጢቆ ተወለደ። አባቱ አለቃ ደስታ ነግዎ ሲባሉ እናቱ ደግሞ ወ/ሮ አፀደማርያም ወንድማገኝ ይባላሉ። ገብረክርስቶስ ደስታ በ1920ዎቹ ወደዚህች ዓለም ብቅ እንዳሉት የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጆች መካከል አንዱ ነው። የሥዕል ጥበብ ገና ሕፃን ሳለ ጀምሮ ውስጡ ተፀነሰ። ገና የአስር ዓመት ልጅ ሳለ ሐረር ውስጥ ተወዳጅ ሥዕሎችን መውለድ የቻለ የጥበብ ክስተት ነበር። እንዲህ እያለ የሥዕል ጥበብ ውስጡ እየዳበረ መጣ። ከዚያም ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋክሊቲ ገባ። ለሁለት ዓመታት ተምሮ አቋረጠ። ቀጥሎም ወደ ጀርመን ሀገር ሔዶ በኮሌኝ የሥዕል አካዳሚ ተማረ። ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያም መጥቶ ማስተማር ጀመረ። በ1955 ዓ.ም የሥዕል አውደ-ርዕይ ሲከፍት በሥራዎቹ ተደንቀው መጥተው የከ

ሃይማኖት እንደ ሕያው ነገር

   “-- በምዕራቡ ዓለም የግልና የማህበራዊ ችግሮች መፍትሔ የሚፈለግላቸው ዘዴዎች በዋናነት በህዝባዊ ምርጫ፣ በዘመናዊ ( ነፃ ) የህክምና አገልግሎት፣ በሃቀኛ የፖሊስ ሃይልና በሚዛናዊ የፍትሕ ስርዓት ነው። በኔ ግምት፣ የዘመናዊነት ዋነኛ መገለጫዎች እነዚህ ሲሆኑ ከእነሱ ጋር ግብግብ መግጠም “ አጉል መንፈራገጥ …” ይሆናል። --”          የሥነ ሕይወት ትምህርት በጣም ሰፊና ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ዋናው መሠረቱ ግን ዝግመተ - ለውጥ (Evolution) የሚባለው ዘርፍ ነው። ምክያቱም ሕይወት ያላቸው ፍጡራን በሙሉ የዝግመተ - ለውጥ አሻራ ስላላቸውና የህጉም ውጤቶች እንደሆኑ ማሳየት ስለሚቻል ነው። የዝግመተ - ለውጥ ዋናው መርህ፣ ተፈጥሯዊ ምርጫ (natural selection) ሲሆን ይህም ግልፅ የሕይወትና ሞት ምርጫ ጉዳይ ነው። ተፈጥሯዊ ምርጫ የሚፈፀመው ባጭሩ እንደሚከተለው ነው። የሚኖሩበትን አካባቢ የተላመዱ ፍጥረታት በደንብ ካልተላመዱት ፍጥረታት የላቀ የመራባት ስኬት (reproductive success) ይኖራቸዋል ( በአንጻራዊ ሁኔታ በቂ ጊዜ፣ በሕይወት የመኖርና ብዙ ዝርያዎችን የማፍራት ዕድል ስላላቸው ) ። ይህ ብቻም አይደለም፤ ተፈጥሮና ፍጥረታት ሁሌም በግብግብ ውስጥ ስለሆኑ፣ የአካባቢው ሁኔታ ( ለምሳሌ፡ - የግብዓቶች መጠንና ዓይነት፣ የአየር ፀባይ …) በተቀየረ ቁጥር፣ ፍጥረታት ያን ሁኔታ የሚለምዱበትን አዲስ ባህርይ ( የሰውነት ክፍልም ሊሆን ይችላል ) በፍጥነት መፍጠርና ለአዲሱ አካባቢ የማያስፈልጉ ( አድካሚ