Posts

Showing posts from January, 2018

"ለማበድ እንኳን ሀገር ያስፈልጋል"

"ለማበድ እንኳን ሀገር ያስፈልጋል" -መጋቢ ሐዲስ እሸቱ (ያሬድ ሹመቴ) የ #ጉዞ_ዓድዋ_4 ተጓዦችን በክብር ለመቀበል ከኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለ ስልጣን ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምሽት ተገኝተው ድንቅ ንግግር ያደረጉትን የመምህራችንን መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ሀሳብ ለንባብ እንዲመች አድርጌ በመፃፍ እነሆ ጋብዤያችኋለሁ። ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ በፌስቡክ መንደራችን ከዳር እስከዳር እንደምናዳርሰው ተስፋ አለኝ። መጋቢ ሀዲስ እሸቱ እንደምን አመሻችሁ? በባከነ ሰዓት ነው (የመጣሁት) የዓድዋ ጦርነት እንኳን የዚህን ያህል ግዜ አልወሰደም። (ሳቅ) ጦርነቱ በአጭሩ ተጠናቀቀ። ስለጦርነቱ ለማውራት ግን አራት ሰዓት አስፈልጎናል። እንግዲህ መናገር እና መዋጋት የተለያየ ነው። መናገር ውጊያ የለውም። ፍልሚያ የለውም። መሞት የለበትም። ሁላችንም ብዙ እንናገራለን እግዚአብሔር ይመስገን። (ረዥም ሳቅ) ቅድም ከነበሩ ተናጋሪዎች ከዲያቆን ዳንኤል ክብረትና ከወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ ንግግሮች ወስጄ (አጋጥሜ) አንድ ነገር ልስፋ። ዳንኤል ከነገረን ቁምነገር አንዱ "በሁሉም ነገር መግባባት አለብን ወይ?" ወ/ሮ ሰሎሜ ደግሞ የነገሩን "ነገሮችን በሙሉ በፖለቲካ መግባባት አለብን ወይ?" ሁለት አይነት ናቸው የተነገሩን። ከስድስት ወር በፊት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ እንደ አጋጣሚ የተናገርኩት ነገር አለ። 'ጣሊያንን ከሀገር ለማስወጣት አባቶቻችን ደማቸውን አፈሰሱ። በግልባጩ ደግሞ ጣሊያን ለመግባት ዛሬ ሜዲትራሊያን ባህር ደማችን እየፈሰሰ ነው" ብዬ ተናግሬ ነበር። (ሳቅ)... ....እንደውም እኔ ጣሊያንን ከምናሸንፍ ምን አልባት ጁቬንቱስ (የእግር ኳስ ቡድንን) አሸንፈን ቢሆን ብዬ አሰብኩ። (ሳ