ወጥቶ የቀረው ኢትዮጵያዊው የጥበብ ሊቅ- ገብረክርስቶስ ደስታ
ለዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ኢትዮጵያዊ ጥበበኛ፣ ኢትዮጵያን እጅግ የሚወዳት፣ በኢትዮጵያ የሥዕል እና የሥነ-ግጥም ዓለም ውስጥ ድምቅምቅ ብሎ ሁሌም ስሙ ስለሚጠራው ስለ ታላቁ ጥበበኛችን ስለ ገብረክርስቶስ ደስታ ነው። ገብረ ክርስቶስ ደስታ “ስሞት ሀገሬ ቅበሩኝ” እያለ በግጥም እየተቀኘ ሲማፀን የኖረ ባለቅኔ ቢሆንም፤ ሞቶ የተቀበረው ግን በባዕድ ሀገር ነው። ገብሬ “ሀገሬ” ብሎ ሲቀኝ እንዲህ አለ፡- ውበት ነው አገሬ ገነት ነው አገሬ ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ ባሳብ እሄዳለሁ ቢሰበርም እግሬ አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ። አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ “ብሞት እሔዳለሁ ከመሬት ብገባ” እያለ የዛሬ 50 ዓመት ግጥም የፃፈ ሰው ዛሬም አፅሙ በምድረ አሜሪካ ነው። ዛሬ ስለ ጥበበኛው ገብረክርስቶስ ደስታ ጥቂት ነጥቦችን እንጨዋወታለን። ገብረክርስቶስ ደስታ ጥቅምት 5 ቀን 1924 ዓ.ም በሐረር ከተማ አደሬ ጢቆ ተወለደ። አባቱ አለቃ ደስታ ነግዎ ሲባሉ እናቱ ደግሞ ወ/ሮ አፀደማርያም ወንድማገኝ ይባላሉ። ገብረክርስቶስ ደስታ በ1920ዎቹ ወደዚህች ዓለም ብቅ እንዳሉት የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጆች መካከል አንዱ ነው። የሥዕል ጥበብ ገና ሕፃን ሳለ ጀምሮ ውስጡ ተፀነሰ። ገና የአስር ዓመት ልጅ ሳለ ሐረር ውስጥ ተወዳጅ ሥዕሎችን መውለድ የቻለ የጥበብ ክስተት ነበር። እንዲህ እያለ የሥዕል ጥበብ ውስጡ እየዳበረ መጣ። ከዚያም ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋክሊቲ ገባ። ለሁለት ዓመታት ተምሮ አቋረጠ። ቀጥሎም ወደ ጀርመን ሀገር ሔዶ በኮሌኝ የሥዕል አካዳሚ ተማረ። ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያም መጥቶ ማስተማር ጀመረ። በ1955 ዓ.ም የሥዕል አውደ-ርዕይ ሲከፍት በሥራዎቹ ተደንቀው መጥተው የከ...
yameral
ReplyDelete