Amazing Ethiopian Edilu&Hirute Wedding Get link Facebook Twitter Pinterest Email Other Apps - March 16, 2018 it is enjoyed these wedding Get link Facebook Twitter Pinterest Email Other Apps Comments
ወጥቶ የቀረው ኢትዮጵያዊው የጥበብ ሊቅ- ገብረክርስቶስ ደስታ - December 31, 2017 ለዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ኢትዮጵያዊ ጥበበኛ፣ ኢትዮጵያን እጅግ የሚወዳት፣ በኢትዮጵያ የሥዕል እና የሥነ-ግጥም ዓለም ውስጥ ድምቅምቅ ብሎ ሁሌም ስሙ ስለሚጠራው ስለ ታላቁ ጥበበኛችን ስለ ገብረክርስቶስ ደስታ ነው። ገብረ ክርስቶስ ደስታ “ስሞት ሀገሬ ቅበሩኝ” እያለ በግጥም እየተቀኘ ሲማፀን የኖረ ባለቅኔ ቢሆንም፤ ሞቶ የተቀበረው ግን በባዕድ ሀገር ነው። ገብሬ “ሀገሬ” ብሎ ሲቀኝ እንዲህ አለ፡- ውበት ነው አገሬ ገነት ነው አገሬ ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ ባሳብ እሄዳለሁ ቢሰበርም እግሬ አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ። አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ “ብሞት እሔዳለሁ ከመሬት ብገባ” እያለ የዛሬ 50 ዓመት ግጥም የፃፈ ሰው ዛሬም አፅሙ በምድረ አሜሪካ ነው። ዛሬ ስለ ጥበበኛው ገብረክርስቶስ ደስታ ጥቂት ነጥቦችን እንጨዋወታለን። ገብረክርስቶስ ደስታ ጥቅምት 5 ቀን 1924 ዓ.ም በሐረር ከተማ አደሬ ጢቆ ተወለደ። አባቱ አለቃ ደስታ ነግዎ ሲባሉ እናቱ ደግሞ ወ/ሮ አፀደማርያም ወንድማገኝ ይባላሉ። ገብረክርስቶስ ደስታ በ1920ዎቹ ወደዚህች ዓለም ብቅ እንዳሉት የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጆች መካከል አንዱ ነው። የሥዕል ጥበብ ገና ሕፃን ሳለ ጀምሮ ውስጡ ተፀነሰ። ገና የአስር ዓመት ልጅ ሳለ ሐረር ውስጥ ተወዳጅ ሥዕሎችን መውለድ የቻለ የጥበብ ክስተት ነበር። እንዲህ እያለ የሥዕል ጥበብ ውስጡ እየዳበረ መጣ። ከዚያም ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋክሊቲ ገባ። ለሁለት ዓመታት ተምሮ አቋረጠ። ቀጥሎም ወደ ጀርመን ሀገር ሔዶ በኮሌኝ የሥዕል አካዳሚ ተማረ። ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያም መጥቶ ማስተማር ጀመረ። በ1955 ዓ.ም የሥዕል አውደ-ርዕይ ሲከፍት በሥራዎቹ ተደንቀው መጥተው የከ Read more
"ለማበድ እንኳን ሀገር ያስፈልጋል" - January 13, 2018 "ለማበድ እንኳን ሀገር ያስፈልጋል" -መጋቢ ሐዲስ እሸቱ (ያሬድ ሹመቴ) የ #ጉዞ_ዓድዋ_4 ተጓዦችን በክብር ለመቀበል ከኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለ ስልጣን ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምሽት ተገኝተው ድንቅ ንግግር ያደረጉትን የመምህራችንን መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ሀሳብ ለንባብ እንዲመች አድርጌ በመፃፍ እነሆ ጋብዤያችኋለሁ። ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ በፌስቡክ መንደራችን ከዳር እስከዳር እንደምናዳርሰው ተስፋ አለኝ። መጋቢ ሀዲስ እሸቱ እንደምን አመሻችሁ? በባከነ ሰዓት ነው (የመጣሁት) የዓድዋ ጦርነት እንኳን የዚህን ያህል ግዜ አልወሰደም። (ሳቅ) ጦርነቱ በአጭሩ ተጠናቀቀ። ስለጦርነቱ ለማውራት ግን አራት ሰዓት አስፈልጎናል። እንግዲህ መናገር እና መዋጋት የተለያየ ነው። መናገር ውጊያ የለውም። ፍልሚያ የለውም። መሞት የለበትም። ሁላችንም ብዙ እንናገራለን እግዚአብሔር ይመስገን። (ረዥም ሳቅ) ቅድም ከነበሩ ተናጋሪዎች ከዲያቆን ዳንኤል ክብረትና ከወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ ንግግሮች ወስጄ (አጋጥሜ) አንድ ነገር ልስፋ። ዳንኤል ከነገረን ቁምነገር አንዱ "በሁሉም ነገር መግባባት አለብን ወይ?" ወ/ሮ ሰሎሜ ደግሞ የነገሩን "ነገሮችን በሙሉ በፖለቲካ መግባባት አለብን ወይ?" ሁለት አይነት ናቸው የተነገሩን። ከስድስት ወር በፊት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ እንደ አጋጣሚ የተናገርኩት ነገር አለ። 'ጣሊያንን ከሀገር ለማስወጣት አባቶቻችን ደማቸውን አፈሰሱ። በግልባጩ ደግሞ ጣሊያን ለመግባት ዛሬ ሜዲትራሊያን ባህር ደማችን እየፈሰሰ ነው" ብዬ ተናግሬ ነበር። (ሳቅ)... ....እንደውም እኔ ጣሊያንን ከምናሸንፍ ምን አልባት ጁቬንቱስ (የእግር ኳስ ቡድንን) አሸንፈን ቢሆን ብዬ አሰብኩ። (ሳ Read more
Comments
Post a Comment