"ለማበድ እንኳን ሀገር ያስፈልጋል"

"ለማበድ እንኳን ሀገር ያስፈልጋል"
-መጋቢ ሐዲስ እሸቱ
(ያሬድ ሹመቴ)
የ #ጉዞ_ዓድዋ_4 ተጓዦችን በክብር ለመቀበል ከኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለ ስልጣን ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምሽት ተገኝተው ድንቅ ንግግር ያደረጉትን የመምህራችንን መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ሀሳብ ለንባብ እንዲመች አድርጌ በመፃፍ እነሆ ጋብዤያችኋለሁ።
ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ በፌስቡክ መንደራችን ከዳር እስከዳር እንደምናዳርሰው ተስፋ አለኝ።
መጋቢ ሀዲስ እሸቱ
እንደምን አመሻችሁ? በባከነ ሰዓት ነው (የመጣሁት) የዓድዋ ጦርነት እንኳን የዚህን ያህል ግዜ አልወሰደም። (ሳቅ) ጦርነቱ በአጭሩ ተጠናቀቀ። ስለጦርነቱ ለማውራት ግን አራት ሰዓት አስፈልጎናል። እንግዲህ መናገር እና መዋጋት የተለያየ ነው። መናገር ውጊያ የለውም። ፍልሚያ የለውም። መሞት የለበትም። ሁላችንም ብዙ እንናገራለን እግዚአብሔር ይመስገን። (ረዥም ሳቅ)
ቅድም ከነበሩ ተናጋሪዎች ከዲያቆን ዳንኤል ክብረትና ከወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ ንግግሮች ወስጄ (አጋጥሜ) አንድ ነገር ልስፋ።
ዳንኤል ከነገረን ቁምነገር አንዱ "በሁሉም ነገር መግባባት አለብን ወይ?"
ወ/ሮ ሰሎሜ ደግሞ የነገሩን "ነገሮችን በሙሉ በፖለቲካ መግባባት አለብን ወይ?"
ሁለት አይነት ናቸው የተነገሩን። ከስድስት ወር በፊት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ እንደ አጋጣሚ የተናገርኩት ነገር አለ። 'ጣሊያንን ከሀገር ለማስወጣት አባቶቻችን ደማቸውን አፈሰሱ። በግልባጩ ደግሞ ጣሊያን ለመግባት ዛሬ ሜዲትራሊያን ባህር ደማችን እየፈሰሰ ነው" ብዬ ተናግሬ ነበር። (ሳቅ)...
....እንደውም እኔ ጣሊያንን ከምናሸንፍ ምን አልባት ጁቬንቱስ (የእግር ኳስ ቡድንን) አሸንፈን ቢሆን ብዬ አሰብኩ። (ሳቅ)..ወይም ኢንተር ሚላንን አሸንፈን ቢሆን ኖሮ የበለጠ ይወራልን ነበር!? ብዬ አሰብኩ!
ቅድም ዳንኤል እንዳለው እኔም ባለፈው እንግሊዝ ሀገር ሔጄ ስሰማ፥ ማንቺስተር ሊቨር ፑል ምናምን የሚባሉት የእግር ኳስ ቡድኖች በሙሉ ለካስ ከተሞች ናቸው። አሁን አንድ ወጣት አግኝታችሁ 'ሊቨር ፖል ምንድነው? ብትሉት 'የእግር ኳስ ቡድን ነው። ነው የሚላችሁ'። ፈረንጆቹ ሳናውቀው የቀበሌዎቻቸውን ስም ያሸመድዱናል። (ረዥም ሳቅ) እነ ሲ ኤም ሲ እነ ኮልፌ እነ መርካቶ ማንም አያውቃቸውም (ምክንያቱም) የኳስ ቡድን የላቸውም።(ረዥም ሳቅ) እናም ዓድዋን ለማስጠራት ዓድዋ የሚባል የኳስ ቡድን ማቋቋም አለብን ወይ? የሚል ሌላ ሀሳብ አለኝ።
ሌላው ደግሞ ጀግንነት አሁንም መሰበክ አለበት። በአለም ላይ ጦርነት እንዲጠፋ መፀለይ፥ ፀሎቱን የመሰማት እድሜ ማራዘም ይመስለኛል። ጦርነት ምክንያታዊ እንዲሆን መፀለይ ነው እንጂ ጦርነት እንዲጠፋ መፀለይ ጅልነት ነው የሚመስለኝ። እንኳን ስንት ቢሊየን ህዝብ ባለበት ዓለም፥ አዳምና ሔዋን ሁለት ሆነው በገነት መስማማት ያልቻሉበትን ህይወት፥ እኛ ከየት አግኝተን ነው በድርድር የምንግባባው...(ሳቅ) ውሸት ነው። ስለዚህ ጀግንነት መሰበክ አለበት።
የዛሬ መቶ ምናምን አመት ጣልያኖችን አሸነፍን። ነገር ግን ጠላቶቻችን ተቀይረው ሊሆን ይችላል እንጂ አሁንም ፈጽሞ ሊጠፉ አይችሉም። ስለዚህ ጀግንነት መሰበክ መነገር አለበት።
በሌላ በኩል ደግሞ የጦሩ መሪዎች ፖለቲከኞቻችን፥ በጥንት ግዜ የነበሩት፥ አፄ ምኒልክ በሉ፥ አፄ ኃይለ ሥላሴ ብንል መንግስቱ ኃይለማሪያም፥ መለስ ዜናዊ በሉ፥ አቶ ኃይለማሪያም፥ እነዚህ ሁሉ መልዓክም ሰይጣንም አይደሉም። ሰዎች ናቸው። ምን ለማለት ነው የፈለግኩት?.... ምክንያቱም ሰይጣን ቢሆን ለምስጋና አይመችም። መልዓክ ቢሆንም ለትችት አይመችም። ሰው ከሆነ ግን ለትችትም ለምስጋናም ይመቻል። (ረዥም ጭብጨባ)
የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ ኔልሰን ማንዴላ በሞቱበት ወቅት ሰሞን አንድ የግዕዝ ቅኔ አቅርቤ ነበር። ምኒልክን እና ማንዴላን አነፃጽሬ። እና አማርኛውን ልንገራችሁ።
ምዕራባውያኑን እኩል አሸነፉ
ምኒልክ በሰይፉ ወ-ማንዴላ ባፉ።
ነበር ያልኩት (ሳቅ) እና ምን ነበር ለማለት የፈለግኩት፥ ምኒልክና ማንዴላ ሁለቱም ጀግኖች ናቸው። ልዩነቱ፥ ማንዴላ በትህትና ደም ሳያፈስ ይቅር በሉን፥ ይቅር ብለናችኋል ብላ!... (ረዥም ሳቅ) በለስላሳ ዲፕሎማሲ፥ አሁን ዜና ስንሰማ ደቡብ አፍሪካ ነፃ ከወጣች 23 ዓመት ሆናት፥ አሁንም ግን ነፃ ወጥተናል ወይ? እያሉ እየጠየቁ ነዎ ሰዎቹ። ድርድሩ ነጮቹ የያዙትን እንደያዙ እንዲቀጥሉ፥ ጥቁሮቹ ግን ባርያ የሚባል ቆሞላቸው በተዘዋዋሪ ባሮች ናቸው። (ሳቅ)
እዚህ አገር ባለሀብቶቻችን በሙሉ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ተክለብርሐን አምባዬ የሚባሉ ባለሀብት አውቃለሁ። ሳሙኤል ታፈሰ የሚባል ሰው አውቃለው። ፀጋዩ የሚባል ሰው አውቃለሁ። ባለሀብቶቻችን በሙሉ ገንዘባቸውን ይስጡም አይስጡ አበሾች ናቸው። እንዴት ደስ ይላል። (ረዥም ጭብጨባ)
ደቡብ አፍሪካ ብትሔዱ ግን እያንዳዱ ሪል ስቴት እያንዳዱ ባንክ እያንዳንዱ ኢንሹራንስ በጆንሰን እና በፒተር የተያዘ ነው። (ሳቅ) ጥቁሩ ምን አልባት ባንክ ቤት ብር ያስቀምን እንደሆነ እንጂ፥ ባንክ ቤት የለውም። በግልባጩ እውነቱን ለመናገር ይሔ የዓድዋ ድል ውጤት ነው! እውነቱን ለመናገር አፄ ምኒልክ የከፈሉት ዋጋ ነው። (ከፍተኛ ጭብጨባ)
አንድ ሰው ጋር በስልክ ሳወራ እንዲህ አለኝ "እንዴት ማንዴላን እና ምኒልክን ታነፃጽራለህ?"
'እንደውም ልንገርህ ይቅርታ አድርግልኝና ምኒልክ ይገዝፉብኛል!! አሁን እንግሊዛውያን ለማንዴላ ለንደን ላይ ዋሽንግተን ላይ ሀውልት እንዲቆምለት እየተደራደሩ ነው። እውነት (ማንዴላ) ጥቁሩን አክብረውት ነው ወይ? አይደለም! ነጮቹ ንብረታቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ። ለዚያ የሚከፈል ዋጋ ነው። (ሳቅና ጭብጨባ) ሌላ ምንም ተዓምር የለውም።
አፄ ምኒልክ ግን አዋርደው፥ ማቅ አልብሰው ስለላኳቸው እስከ አሁን ድረስ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንድትኖር የሚፈልጉ አይመስለኝም።
እንደተባለው በሁሉም ነገር መግባባት የለብንም። በወረደ አስተሳሰብ፥ በቋንቋ መጠለፍ የለብንም። መንግስት ክልልን ሲያቋቁም ለአስተዳደር እንዲመች እንጂ ለአስተሳሰብ ክልል አልተመደበም። (ጭብጨባ) አሁን ብዙዎቹ አስተሳሰባቸው ክልላዊ ሆኖባቸው ሲንገላቱ እንመለከታለን።
ሌላው ደግሞ ለአክሱም ሐውልት የሰጠነውን ክብር ቀነስ አድርገን፥ አክሱም ከተማ ላሉት ለነ ጎይቶም ለነ ሐጎስ፥ በዓድዋ ድል እንደተመካነው ሐዳስን አብርሐትን አስገዶምን እናውቃቸዋለን ወይ? የወንዶ ገነትን አቡካዶና ፓፓዬ እየበላን የወንዶ ገነትን ገበሬ ንቆ የት ሊገባ ነው? የጎጃምን ማርና ቅቤ እየበሉ ጎጃምን ቆምጬ ማለት ያዋጣል ወይ? (ረዥም ሳቅ)... ይሔ እየመረረን የምንጠጣው ሀቅ ነው። እኔ አሁን የሚጠቅመንን ነው የምነግራችሁ። የወለጋን ወርቅና ቡናን እየፈለግን እነቶሎሳን ንቆ የት ይገባል?
መግባባት ያስፈልጋል። የአሁኑ ጦርነት የአስተሳሰብ ጦርነት ነው። የአመለካከት ጦርነት ነው። ጽዳት ማለት በህሊና ነው። እኔ በቀደም ሰዎቹ ቆሻሻ ተጭኗቸው አለቁ ሲባል፥ 'ኣረ በየቢሮው ስንት ቆሻሻ የተጫነው ጭንቅላት አለ አልኩኝ' እኔማ። እንደው እስካቫተር የማያነሳው ስንት ቆሻሻ አለ እውነት ለመናገር። እዚያው ከቆሻሻው ቦታ አንድ ሰው ላዳ ተከራይቶ ዘርፎ ሊወጣ ሲል ተያዘ አሉ። እኛ አላየነውም እንጂ ይሔ ሰውዬ ጭንቅላቱ ላይ ቆሻሻ ተንዶበታል። (ሳቅ)
ስለዚህ የሚዲያ ሰዎች፥ የፖለቲካ ሰዎች፥ የሥነጽሁፍ ሰዎች፥ የኪነ-ጠበብ 

Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

ወጥቶ የቀረው ኢትዮጵያዊው የጥበብ ሊቅ- ገብረክርስቶስ ደስታ